Saturday, February 9

ወላይተኛ ቋንቋ እና ወላይታ /በኢትዮጵያና በደቡብ


'''➊✍ወላይትኛ''' በ[[ኢትዮጵያ]] በተጠቃሚ ብዛት በ4ኛነት የሚመደብና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሌሎቹ ተቀራራቢ ቋንቋዎች ምንጭ ነው። ወላይትኛ ከሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በፊት የመጀመሪያው የ[[ላቲን ፊደል]] [[መጽኃፍ ቅዱስ]] ታትሞበታል። ከወላይትኛ ጋር ዝምድና ያላቸው ሌሎች ቋንቋዎች [[ጋሞ-ጎፋ-ዳውሮ]] እና ኩሎና ኮንታ ናቸው። ባሁኑ ጊዜ በሥልጣን ላይ ያለው የ[[ኢሕአዴግ]] መንግሥት እነኚህን ተቀራራቢ ቋንቋዎች ነገር ግን 25% ትርጓሜዎቻቸው እርስ በርሳቸው በፍጹም የማይገናናኙትን <ዎጋጎዳ> በማለት አዲስ ስያሜ በመስጠት የ1ኛ ደረጃ መማሪያ መጽሃፍ አዘጋጀ። ይሁን እንጂ በተለይ በወላይታ ተወላጆች ዘንድ ኃይለኛ ቁጣን አስነስቶ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን በማጣታቸው ጉዳዩ የዓለምን ትኩረት ስቦ ነበር። ለምሣሌ ያህል፡ <ኦታ> ማለት በወላይትኛ ሥራ ማለት ሲሆን በጎሙኛ ግን [[ግብረ ሥጋ ግንኙነት]] የሚል ትርጓሜ ስላለው ለኅብረተሰቡ ያልተለመደና እጅግ አስነዋሪ ቃል ነው። <ቦግስ> ማለት በወላይተኛ አፍጥኗል ሲሆን በዳውሮኛ [ሩካቤ ስጋ ፈፅሟል] የሚል ትርጓሜ ይሰጣል። በአንጻሩ ግን አብዛኛው ቃል ቢመሳሰልም በመጽኃፍ ደረጃ ታትሞ ለልጆች ትምህርት እንዲውል ገዢው መንግሥት በቂ ጥናት ስላላደረገ በቂ ግንዛቤ አልነበረውም። ተቀባይነት ሳይኖረዉም ቀረ ታርካዊ ስህተትም ተደርጎ ይወሰዳል። ወንድማማቾች እና እህታማቾች የሆኑ ወላይታ ፣ጋሞ፤ጎፋና ዳዉሮ ህዝቦችንም አቃቅሯል።ሆኖም ወላይታዎች ወላይተኛን የአፍ መፍቻና ሥራ ቋንቋ አድርገው የቀጠሉት ከብዙ መስዕዋትነት በኃላ ነዉ። አማረኛ፣ኦሮምኛንና ሶማሊኛን ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ የሚገኘው ወላይተኛ ቋንቋ ከሌሎች ደቡብ ብሔረሰቦች ቋንቋዎች ግን ግንባርቀደም ነው። {{መዋቅር}} [[መደብ:ኦሞቲክ ቋንቋዎች]] ➋✍ወላይታ በቀድሞ ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ባሁኑ ደቡብ ክልል የሚገኝ ና የራሱ የሆነ ቋንቋና ባህል ያለው ሕዝብ ሲሆን ከ ሲዳማ፡ ከ ከምባታ፡ ከ ሃዲያና ተመሳሳይ ቋንቋ ከሚናገሩ ከ ኩሎ ኮንታ ከ ጎፋና ጋሞ ሕዝብ ጋር ይዋሰናል። ወላይታ ህዝቡ በጣም የተደባለቀ(ዉስብስብ) ሲሆን በከተማ አከባቢ ልቆ የሚገኝ ኃይማኖት ኦርቶዶክስ ይሁን እንጂ በጠቅላላ አውራጃው ፕሮቴስታንትና እስልምና እምነት እየተስፋፋ ነው። የወላይታ ዞን አስራ ሁለት ወረዳዎች አሉት። እነሱም፦ 1ኛ - ዳሞት ጋሌ ዋና ከተማው ቦዲቲ፡ 2ኛ -ዳሞት ወይዴ ዋና ከተማው፦ በደሳ፡ 3ኛ -ቦሎሶ ሶሬ ዋና ከተማው አረካ፡ 4ኛ - ሁምቦ ዋና ከተማው ጠበላ፡ 5ኛ - ኦፋ ዋና ከተማው ገሱባ፡ 6ኛ- ሶዶ ዙሪያ ዋና ከተማው ሶዶ፡ 7ኛ- ኮይሻ ዋና ከተማው በሌ፡ 8ኛ- ቦሎሶ ቦምበ ዋና ከተማው ቦምበ እድገት፡ 9ኛ- ዳሞት ሶሬ ዋና ከተማው ጉኑኖ፡ 10ኛ- ዱጉና ፋንጎ ዋና ከተማው ቢጣና፡ 11ኛ ዳሞት ፉላሳ ዋና ከተማው ሻንቶ፡ እና 12ኛ ኪንዶ ዲዳዬ ዋና ከተማው ሀላለ ናቸው። ወላይታ ከደቡብ ካሉት አከባቢዎች በትምህርት፡ በልማትና በማህበራዊ ሁኔታዎች ልቆ ሊገኝበት የቻለበት ሁኔታዎች ይታያል። ይህም የሆነበት ምክንያት በ ቀደማዊ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ምዕራባዊያን በብዛት ገብተው የአከባቢውን ሕዝብ ከ መጽሓፍ ቅዱስ ጋር የቀለም ትምህርት አጣምረው ስለሰጡ እድሉን በመጠኑም ቢሆን በመጠቀማቸውና በየጊዜው በአከባቢው የሚመደቡ አስተዳዳሪዎች ጠንካራ በመሆናቸው ነው ይባላል። በቀድሞ ዘመን በወላይታ በርካታ ምሁራን ብቅ ብቅ ብለው ነበር። ከነዚህም ምሁራን በደቡብ ኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ዶክተርና የጦር ጄኔራል ለመሆኑ የበቁ ብ/ ጄኔራል ዶ/ር ጋጋ ኤልጆ በአብይነት ሲጠቀሱ ፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ካንገት በላይ ስፔሻሊስት ዶ/ር ታዲዮስ ሙንኤ ; ኢትዮጵያ ካሏት ጥቂት የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ቀለሙ ደስታ ፡ አሜሪካን አገር በ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ፍሎሪዳ ታዋቂ ሓኪምና ረዳት ፕሮፌስር የሆኑ ዶ/ር ይስሓቅ ዳልኬ ናቸው።[1] ዶ/ር ይስሓቅ በትምህርት ውጤታቸው ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ልቀው በመገኘታቸው ከአጼ ኃይለስላሴ እጅ የወርቅ ሰዓት የተሸለሙ 2ኛው የወላይታ ተወላጅ ሲሆኑ ዳዊት ጦሼ ደግሞ የመጀመሪያው ናቸው። የወላይታ ታሪክ ሲወሳ የወላይታ የልማት አባት በሚል የሚታወቁ ዳጃ/ች ወ/ሰማዕት ስም ሁሌም አብሮ ይወሳል። ደ/ች ወ/ሰማዕት በአስተዳዳሪነት በቆዩበት በአጼ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ብዙ የልማት ስራዎችን አከናውነዋል። ከሰሯቸው አበይት ስራዎቻቸውም ፦ በጊዜው የነበሩትን ሰባቱንም ወረዳዎች የሚያገናኝ መንገድ አሰርተዋል። በሚሲዮናዊያን አማካኝነት የመጀመሪያውን የደቡብ ሆስፒታል አስገንብተዋል። ወላይታን ከምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያገናኝና 90 ሜትር ርዝመት ያለውን ታሪካዊውን የኦሞ ድልድይ አሰርተዋል። ወጣቱ ትርፍ ጊዜውን የሚያሳልፈበትን ወወክማ የወጣቶች መንደር ከዘመናዊ በተ-መጻሕፍት ጋር አሰርተዋል። በሶዶ ከተማ ዘመናዊ የገበያ አዳራሽ ከማሰራታቸው ነው። ከይርጋለም ቀጥሎ በደቡብ የመጀመሪያውን ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አሰርተዋል። ደ/ች ወ/ሰማዕት በወቅቱ ማንም ወጣት የሆነ መንገድ ዳር ቆሞ ሲያወራ ካዩ ይበሳጩ እንደነበርና ከመኪናቸው ወርደው ስራ እንዲሰሩ ወይም ት/ቤት እንዲሄዱ ይመክሩም እንደነበር ይነገርላቸዋል። ባሁኑ ጊዜ ባገር ውስጥና ከአገር ውጭ በተሳተፉበት የሙያ ዘርፍ ሁሉ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር አንቱታን የተጎናጸፉ የወላይታ ተወላጆች ብዛት በርካታ ነው። አቶ ቦጋለ ዋላሎ እና ዋና ዋጌሾ በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ትምህርትን ያስፋፉ የወላይታ ተወላጆች ናቸዉ።

No comments:

Featured Posts

“ግብፅ ግድቡን የሚመታ ራፋል የተባለ የጦር አውሮፕላን ገዝታ ነበር” የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም የተወለዱት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ የጁ ወረዳ በምትገኝ አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው። የልጅነት ጊዚያቸው...

Blogger