Wednesday, September 24

“ግብፅ ግድቡን የሚመታ ራፋል የተባለ የጦር አውሮፕላን ገዝታ ነበር” የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም የተወለዱት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ የጁ ወረዳ በምትገኝ አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው። የልጅነት ጊዚያቸውን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ አሳልፈዋል። የሆነ አጋጣሚ ግን ወደ ሳውዲ እንዲጓዙ ዕድል ሰጣቸው። በሳውዲም ትምህርታቸውን ተከታተሉ፤ አረብኛ ቋንቋን በደንብ ተማሩ እና የአረቡ ሀገራትን በውል እንዲረዱም እድሉን አገኙ። ግብፅን በደንብ ያውቃሉ፤ በተለይ በሱዳን እና በአካባቢው ለ30 ዓመታት ኑረዋል። በዓባይ እና በኢትዮጵያ ዙሪያ በተለያዩ መድረኮች ሲሟገቱም እናውቃቸዋለን። የዛሬ የበኩር እንግዳችን የታሪክ ምሁር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር አደም ካሚል ናቸው። የህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ጫናዎችን በተመለከተ ቆይታ አድርገናል ለአንባቢያንም እንዲህ አቅርበነዋል። በዓባይ ወንዝ ላይ ግብፅ እና ሱዳን ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ሀሳብ ምንድን ነው? ሱዳን እና ግብፅ ኢትዮጵያ የዓባይን ውኃ መጠቀም የለባትም፤ የእኛ ብቻ የፈጣሪ ስጦታ ነው ብለው ነው የሚያስቡት። ስለዚህም ከጥንት ጀምረው በሚዲያቸውም፣ በወጋቸውም በባሕላቸውም ዓባይ ማለት ፈጣሪ ለእኛ የቸረን ገፀ በረከታችን ነው ብለው ስለሚያምኑ የኢትዮጵያ ዓባይን መጠቀም ሰላም ይነሳቸዋል። ለምሳሌ አንዲት የግብፅ እናት ልጅ ወልዳ ስታሳደግ ልጇን ጡት ስታጠባው የሚጠባው ወተት ፈጣሪ በዓባይ በኩል እንደሰጠው እየነገረች እያስተማረች ነው የምታሳድገው። ይሄ ዓባይ ውኃ ምን ያህል በውስጣቸው እንደሰሠርፀ እና ለትውልዱ በምን መንገድ እያስተላለፉ እንደሆነ ያስረዳል። በግብፆች በኩል እንዲህ ከሆነ በኢትዮጵያ በኩልስ ስለዓባይ ወንዝ ያለው አመለካከት ምን ይመስላል? ወደኛ ስንመጣ ዓባይ የራሳቸን ንብረት ሆኖ 86 በመቶ ውኃውን እያዋጣን ግን ዓባይ ግንድ ይዞ ይዞራል የሚል የሚያስቆጭ አመለካከት ተጭኖን ነው ለዘመናት የኖርነው። ይሄ “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” የሆነ አመለካከት ለዓመታት ሰርፆብን እንዲኖር ግብፆች የተለያዩ ሴራዎችን በዘመናት መካከል ሲፈፅሙብን ቆይተዋል። የእዛ ዳፋ በዓባይ ወንዝ ላይ የበይ ተመልካች አድርጎን ዓባይን ይዘን በድህነት እና በጨለማ ለዘመናት እንድንኖር አድርጎናል። ግብፆች በኢትዮጵያ ላይ ሴራ የሚፈፅሙብን በምን መንገድ ነበር? አንደኛው ሴራ ፈጣሪ በሰጠን ቀናት ሥራ እንዳንሠራ የሴራ አመለካከት ይጭኑብናል። በግብፅ ውስጥ ያለሥራ የሚያልፍ ቀን የለም ፤ የማይሠራበት ዕለት የለም። ግብፅ ውስጥ የክርስትና እምነት ተከታዮች አሉ። እንደሚታወቀውም የግብፅ አብያተክርስትያናት አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያን አብያተክርስትያናት ያስተዳድሩ ነበር። አንድ ወቅት ከግብፅ ፓትሪያሪክ ጋር በአረበኛ ስንወያይ “በእናንት ሀይማኖት በዓመት ስንት ቀን ነው በዓል የምታከብሩት? ሥራ የማትሠሩት?” ብዬ ጠይቄአቸው፤ የሰጡኝ መልስ በእኛ “ ሥራ የማያሠራ በዓል የሚባል የለም” የሚል ነበር። እኔ ጥያቄዬን አስከትዬ “ታዲያ ለምን እኛን በበዓል ምክንያት በዓመት 124 ቀናት ብቻ እንድንሠራ አደረጋችሁ? ለምንስ ይሄንን አስተማራችሁ” አልኳቸው፤ የሰጡኝ መልስ አጭር ነበር “ እናንተማ እንኳን ሠርታችሁ ሳትሠሩም ሰላም እያሳጣችሁን ነው የሚል ነበር። በአጠቃላይ ግብፆች በእኛ ላይ ከሀይማኖት ጨምሮ ብዙ ሴራዎችን ሲያሴሩብን ነው የኖሩት። ከዚህ ውጭ በግብጽ መሪዎች በኩል የተሠራው ሴራ በምን ይገለፃል? ከታሪክ አኳያ? የግብፅ መሪዎች በኢትዮጵያ ላይ ሴራና ተንኮል ከመጠምጠም ለአፍታ ተዘናግተው አያቁም። ከጥንት ጀምሮ የግብፅ መሪዎች ኢትዮጵያ ጠንካራ እንዳትሆን እንዲሁም አንድነት እንዳይኖራት ያላደረጉት ጥረት ያልፈፀሙትም ሴራ የለም። ለምሳሌ በፕሬዝደንት መሀመድ አሊባሽ አማካኝነት በ1868 እ.አ.አ ዐፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዝ ጋር እንዲጋጩና በመጨረሻም በጀግንነት ራሳቸውን እንዲሰው ግብፆች ከንግሥት ቪክቶሪያ ጋር በመተባበር ያሴሩት ሴራም ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ግብፆች 20ሺህ ወታደሮች አልቀውባቸው ተመለሱ እንጂ በ1875-1876 በኢትዮጵያ ላይ የፈፀሙት የጦር ዘመቻም የሴራቸው ህያው ማሳያ ነው። ከዓባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ የግብጽ መሪዎች የፈፀሙት ደባስ እንዴት ይገለፃል? ፕሬዝደንት ጋማል አብድል ናስር በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት አልከፍትም፤ ግን ግድብ እገድባለሁ ብሎ ተነሳ። ከዚያም የእኛን የዓባይን ወንዝ ተጠቅሞ ውኃውን አከማችቶ አስዋን ግድብን ገደበ። ግብጾች የእኛን ውኃ አከማችተው መጠቀም ጀመሩ። ሌላው የግብፅ ፕሬዝደንት አንዋር ሳዳት ደግሞ ኢትዮጵያ ስለግድብ ጥናት እያደረገች መሆኑን ሲሰማ በአደባባይ ወጥቶ “ ኢትዮጵያ ግድብ እገነባለሁ ብላ ከተነሳች ኃይሌን አሟጥጬ በመጠቀም ኢትዮጵያን አጠፋታለሁ” ብሎ ዝቶ ፎክሮ እንደነበረም ታሪክ ምስክር ነው። ሌላው በሆስኒሙባረከ ዘመን ደግሞ ግብፅ ከፍተኛ የጦር ጄነራል ወደ ሱዳን አልበሽር ልካ ኢትዮጵያን ለመምታት የወታደር ካምፕ የማቋቁምበት ቦታ ይሰጠኝ ስትልም ጠይቃ ነበር። በወቅቱ አልበሽር የደቡብ ሱዳን አስቸጋሪ ጉዳይ ስለነበረበት ከኢትዮጵያ ጋር ላለመጋጨትም በማሰብ የግብፅን ጥያቄ አልተቀበለውም ነበር። ሌላው በፕሬዝደንት ሙርሲ ዘመን ግንቦት 26 2005 ዓ.ም እኛ የግድቡን መሰረት ጥለን ነበር። ሙርሲ ካቢኔአቸውን ጠርተው አምስት ዕቅድ አወጡ፤ በእቅዳቸውም ኤርትራን ከማስታጠቅ ጀምሮ የኦጋዴን ነፃ አውጪ ኃይሎችን በማጠናከር ኢትዮጵያን እንዲወጉ ማድረግን አካትተው ነበር። እኛ የህዳሴውን ግድብ ግንባታውን ከጀመርን በኃላ የግብፆች የማደናቀፍ ተግባር እስከምን ደርሶ ነበር? እኛ ግንባታውን ስናካሂድ የግብፅ ፕሬዝደንት አልሲሲ ነበሩ። አልሲሲ የሚያስቡት ኢትዮጵያ በራሷ አቅም አትገነባውም የሚል የንቀት የትዕቢት ሀሳብ ነበር። ከዚህ ሀሳባቸው የተነሳ በዓለም በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ግብፃዊያንን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቀፍ ዘመቻን ማቀጣጠል እንደ ሁነኛ መሳሪያ መጠቀም ጀመሩ። በአውሮፓ ከ150ሺህ በላይ ግብፃዊ ሀኪሞች አሉ፤ የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች ሲኤንኤን እና ቢቢሲን ጨምሮ በግብፆች ይዘወራሉ፤ በግብፅም ከ4ሺህ በላይ ሚዲያዎች አሉ፤ እንዲሁም 800 ሺህ ግብፃዊያን በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው ይሠራሉ። ይህንን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አልሲሲ የኢትዮጵያን የግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ዓለማቀፍ ዘመቻን መጠቀም ምርጫ አድርገው ተገበሩት። በዚህ ሳቢያ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዓለም በሯን እንድትዘጋብን አደረጉ። 30 ነጥብ አራት ቢሊዮን ዶላር እንድናጣም ማድረግ ቻሉ። የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብስ ሴራውን ለማክሸፍ ምን ዘየደ ? በዚህ ወቅት በመሪዎች አማካኝነት የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት እንደ ንብ መንጋ ሆ! ብሎ ተነስቶ በጉልበቱም በዕውቀቱም በገንዘቡም ለግድቡ ርብርብ ማድረግ ጀመረ። የሚገርመው ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን የግድቡን ግንባታ 40 በመቶ አስክናደርስ ድረስ የግብፅ መሪዎች “በራሳቸው አቅም አይሠሩትም” በሚል ትዕቢት ውስጥ ነበሩ። ግብፅ የዓለም ሀገራትን ለማሳመን የተጠቀመችው ምንድን ነው? ግብፆች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የዓለም ሀገራትን ከጎኗ ለማሰለፍ እና ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ለመውሰድ 560 ጊዜ ስብሰባ አድርገዋል። 1850 ጊዜ በኢትዮጵያ ግድብ ላይ ሴራን የሚጠነስሱ ሴሚናሮችን አካሂደዋል። ከዚህ በተጨማሪም 222 መጽሐፎች በአረብኛ ቋንቋ ተጽፈው በዓለም ተሰራጭተዋል። ይህን ሁሉ ደባ ሲፈፀም ግን በመካከለኛው ምስራቅ የነበሩ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች አረብኛ ቋንቋን በውል የሚረዱ እና የሚናገሩም አልነበሩም። በዚህም ምክንያት ሴራውን በሚገባ ሊረዱና በጊዜው ሊያከሽፉት አልቻሉም ነበር። ኢትዮጵያ ጫናዎችን እየተቋቋመች የግድቡን ግንባታ ስትቀጥል ግብፅ ሌላ የጉልበት ውጥን አፀደቀች፤ የህዳሴው ግድብ በጦር አውሮፕላን ይመታ የሚል። ግድቡን የሚመታ ራፋል የተባለ ዘመናዊ የሆነ የጦር አውሮፕላን በብዙ ሚሊዮን ዶላር ተገዛ። ይህ አውሮፕላን ከግብፅ አስከ ህዳሴው ግድብ ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ነዳጅ ከ2ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዞ ግድቡን እንዲያፈነዳ ለአየር ኃይላቸው አዛዣ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቶም ነበር። ይሁንና በብዙ ሚሊዮን ዶላር የገዙት የጦር አውሮፕላን ሳይነሳ የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት ተካሄደ። ግድቡ ውኃ መቋጠር ሲጀምር ስጋታቸው እየጨመረ መጣ፤ በመካከላቸውም መከፋፈል ተጀመረ። አሜሪካ የሚኖሩ የግብፅ መንግሥት ተቃዋሚዎችም ከኢትዮጵያ ጋር በሰላም ብቻ ችግሩ መፈታት አለበት እያሉ እንቅስቃሴ ጀመሩ። ጎን ለጎንም ታሪካዊው ስምምነት መጣስ የለበትም እያሉ ዘመቻም ከፈቱ፡፡ ኢትዮጵያም የቀኝ ግዛት ውልን አልቀበልም እኔ አልተሳተፍኩበትምና በማለት ፀናች። ግብፆች ከአፍሪካዊነት ይልቅ አረብነት ላይ ይንጠለጠላሉ እና የዓባይ ውኃን ጉዳይ ወደ ፀጥታው ጉዳይ ምክር ቤት ሲወስዱት መቆየታቸው ይታወሳል። በፀጥታው ምክር ቤት የሚቀርቡ ጉዳዮች የድንበር ግጭት እና መሰል ጉዳዮች ሲሆኑ የውኃ ጉዳይ ግን በታሪክ የፀጥታው ምክር ቤት ቀርቦ አያቅም። ቢሆንም ግን የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ወደ አፍሪካ ህብረት ተመልሳችሁ ጉዳያችሁን ፍቱ የሚል ሆነ። ግብፆች ግን ተገደው ወደ አፍሪካ ህብረት ከመጡ በኃላ የአሜሪካ እና የምዕራባዊያን ታዛቢዎች ይሳተፉ፤ በበጋም ሆነ በክረምት የዓባይን የውሃ ልቀት የግብፅ ባለሙያ መቆጣጠር አለበት የሚል ሆነ። ይህ ሀሳባቸው ግን በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነትን አላገኘም። ሌላ የሚጨምሩልን ሀሳብ ካለ? በግድቡ ዙሪያ ከሀገራችን ብዙ ይጠበቃል እና ሁላችንም እንበርታ። ለነበረን ቆይታ ከልብ እናመሰግናለን? እኔም ከልብ አመሰግናለሁ! (ግርማ ሙሉጌታ) በኲር የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

Friday, August 7

Dessie Advertisements : ወላይተኛ ቋንቋ እና ወላይታ /በኢትዮጵያና በደቡብ

Dessie Advertisements : ወላይተኛ ቋንቋ እና ወላይታ /በኢትዮጵያና በደቡብ: '''➊✍ወላይትኛ''' በ[[ኢትዮጵያ]] በተጠቃሚ ብዛት በ4ኛነት የሚመደብና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሌሎቹ ተቀራራቢ ቋንቋዎች ምንጭ ...

Thursday, August 15

Monday, July 29

ወቅታዊ ሁኔታችን በሚመለከት የወላይታ ወጣቶች ያወጡት ባለ 11ነጥብ የአቋም መግለጫ

የዎላይታ ዬላጋ አቋም መግለጫ
---------------------------------------
የዎላይታ ሕዝብ ቀድሞ የሰለጠነና የተማረ ብሎም ደቡብ
ኢትዮጵያ በትምህርትና በወንገል ያነጸ ሥልጡን ሕዝብ ነው፡፡
ዎላይታ በደቡብ አካባቢ ዘመናዊ ትምህርትን ቀድሞ
ከመጀመርም ባሻገር እንደ ቦጋለ ዋለሉ አይነት የደቡብ ኢትዮጵያ
አብሪ ኮከብ ያፈራች ከአካባቢው ኋላ ቀርነትና ድንቁርና
የሚያርቅ ዘመናዊ ትምህርትን ያስተዋወቀች የሥልጣኔ
መናኻሪያ የሆነች ናት፡፡ ዘመናዊ የመንግሥት መዋቅር
ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የነበራት ማለትም ካዎ(ንጉሥ)፣
ቡሻሻ (አልጋ ወራሽ)፣ ዱቢያ ( አማማይ/ቃለ መሀላ አስፈጻሚ)፣
ዛካራ ጉዳ( ትዕዛዛ አስተላላፊ ጽህፈት ቤት)፣ ዛባ ዳና( የንብረት
ቁጥጥር ሥራስፈጻሚ )፣ ባሊሞላ ( የህዝብ ምክር ቤት)
፣ቅርናጃ( የንጉሥ ግቢ አስተዳዳሪ/ሚኒስቴር) እራሻ ( ጥገናና
ዕድሳት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ) ፣ ዴንቻ ( የደሃ ዕንባ ጠባቂ ተቋም)፣
ወዳላ ጋንጂያ( መገናኛ ብዙሃን ሃላፊ)፣ ሚጣ ሞጮና ( የአገር
ውስጥ ደህነትና የመንግሥት ግንኙነት ጉዳዮች ሚኒስትር)፣ ካሮ
ሞጮና( የፕሮቶኮል ጉዳይ ሚኒስትር ) ፣ ጋና (አምባሳደር)፣
ወሼ ሞጮና (የመከለከያ ሚኒስቴር)፣ መንዲዳ ኦቾሏ (ደንና
ዱር ልማት ሚኒስትር )፣ አላና ዳና ( የወረዳ አስተዳዳር) ፣
አሩዋ (የእንስሳ ሀብት ልማት ሚኒስሰትር) ፣ ዳና (ጭቃ ሹም) ፣
ጣጬ ሞጮና (ፌዴራል ፖሊስ) ፣ ማያ ( ለቤተ መንግሥት ንብ
አርቢ) ፣ ሁዱጋ (የቀበሌ ተጠሪ፣ ልቀመንበር) ፣ ቶንዲያ
( የንዑስ ቀበሌ ኃላፊ ) እና አዱማ ( የሰፈር ሹም) የነበረው
ሕዝብ ነው ዎላይታ፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዘኛው የአለማችን
አካባቢዎች ግብይትን በአይነት ያደርግ በነበረበት ወቅት ማርጯ
የተሰኘ ገንዘብ አፈር ብርን ከአፈር ለይቶና አንጥሮ የብር ገንዘብ
ወይም ማርጯ የነበረው ታለቅ ሕዝብ ነው፡፡ በተለይ በጊው
ከብር የሚሰሩ ሀሰተኛ ማርጯ ወይም ፎርጅድ ገንዘብ የመለያ
ስልትም በመቀየስ ጥቅም ላይ ያዋለ ሕዝብ ነው፡፡
የራሱ መከላከያ የነበረውና ጠንካራ የፓሊስ ተቋም የነበረው
የዎላይታ ሕዝብ ታላቅ ሕዝብ ነው ፡፡ በተለይ ከወራሪ ጋር
በሚደረገው ውጊያ እንደ ንብ ያሉ ባዮሎካል መሳሪያም ጭምር
ጥቅም ላይ ያዋለ ሕዝብ ነው፡፡ የዎላይታ ሕዝብ ለነጻነቱ
ከመታገል ቦዝኖ የማያውቅ ነው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ከዎላይታ
ጋር ባደረገችው ጦርነት የተሳተፉ ጀነራሎች እያንዳንዳቸውን
ብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የዎላይታ መከላከያ አባላትን በምርኮ
በመውሰዳቸው ወደ አድዋ ስዘምቱ እንደ እራሳቸው ሶር
አድርገው ማሰለፋቸው እንዳለ ሆኖ ከመቶ ሰማኒያ ሺህ
የሚበልጥ የዎላይታ መከላከያ በሚኒሊክ በምርኮ ተወስዶ
በአዲዋ ጦርነት ፊት ለፊት እንዲቆም ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ
ካዎ ጦና እንደ ማነኛው ጀነራል የራሱን ጦር እንዲልክ
በተጠየቀው መሰረት በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን ወደ አዲዋ
ልኳል፡፡ በአዲዋ ጦርነት ወቅት ጥረ ሥጋ የመብላት ባህል
የነበረው ዎላይታዊያን ለስንቅ በጨው የታሸና ሳይበሰብስ
ለወራት ሥጋን የማቆየት የቆየ የዎላይታን ባህል ተጠቅመው
ያዘጋጁትን ጥረ ሥራ ሲመገቡ ያዩ ጣሊያናዊያን የኢትይጵያ
ሰራዊት የሰው ሥጋ በጥረ ስበሉ አይተናልና ፈርተናል
ማለታቸውን በጊዜ እቦታው የነበረ ጣሊያናዊ መናገራቸውም
ጭምር ይነገራል፡፡
የዎላይታ ሕዝብ ጀግንነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በታታሪነቱና ሥራ
ወዳድነቱም የሚታወቅ ሕዝብ ነው፡፡ ዎላይታ ሥራ
አይመርጥም፡፡ በሥራ የማይለግምና በተሰማራበት በማንኛውም
መስክ ውጤታማና አድምቶ በመስራት የሚያወቅ ሕዝብ ነው፡፡
ሥራዎችን በጥብቅ ዲስፕልን ከመምራት ባሻገር በእውቀትና
በቁጥርጠኝነት በማከናወን የሚታወቅ ሕዝብም ነው፡፡
የዎላይታ ሕዝብ ሌሎችን አቃፊና ሰብሳቢ በመሆኑም የሚታወቅ
ሕዝብ ነው፡፡ በዎላይታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጎጆ
ቀልሰውና ሐብት አፍርተው ምንም አይነት እነግድነት
ሳይሰማቸው ይኖራሉ፡፡ ዎላይታ ኑ እንጂ ሂዱ ወይም ውጡ
የማይል(inclusive society) ሕዝብ ነው፡፡ የዎላይታ መናገሻ
የሆነችው ሶዶ(ዳሞታ) ለዘመናት የበርካታ ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መኖሪያነት የሚትታወቅ ከመሆኑም በላይ
እንደበታቸው ሳይሳቀቁ ሐብት ያፈሩባትና እያፈሩባትም ያለች
ከተማ መሆኗ ለዚሁ ጥሩ ማሳያ ናት፡፡
የዎላይታ ሕዝብ ታሪክ በርካታ የመረጃ ምንጮች እንደሚጠቁሞ
ከሆነ ከስድስት እስከ ስምንት ሺህ ዕድሜ ያለው እንደሆነ
ቢገመትም ሁሉም የሚስማማበት የ50 ነገስታት መናገሻ
እንደሆነች ነው፡፡ በዚህም መሰረት አምስት የተለያዩ ሥርወ
መንግሥታት በትረ ሥልጣንን የሚጨብጡ የየራሳቸው ነገስታት
የነበሯ አገር የነበረው ሕዝብ ሕዝብ ነው የዎላይታ ሕዝብ፡፡ ይህ
ታሪካዊ ገናናነት የዎላይታን መንግስት ገርስሶ ወደ ኢትዮጵያ
ለመቀላቀል አጸ ሚኒሊክ ባካሄዱት ሰባት ዓመት በፈጀ ኢትዮ-
ዎላይታ ጦርነት የዎላይታ አገር መከላከያ ተሰብሮና መንግስቱም
ተገርስሶ ወደ ኢትዮጵያ የተቀላቀለ ሕዝብም ነው፡፡
ምንም እንኳ በጉልበት ወደ ኢትጵያ የተቀላቀለ ቢሆንም
በኢትዮጵያዊ አንዲነት በጽኑ አቋምና እምነት አገርን ከውጭ
ወራሪ ለመከላከል በተደረገው ተጋድሎ ከፍተኛውን ሚና
ተጫውቶ የለፋ ማረሻ ግድግድዳ ላይ ተረስቶ ያልለፋው ማንኪያ
ገንፎ ላይ ይሰካል እንደሚል የዎላይታ ምሳሌያዊ አገላለጽ
ትንሽም እውቅና ሳይሰጠው በኢትዮጵያ ታሪክ የተገለለ ሕዝብም
ነው የዎላይታ ሕዝብ፡፡
እንግዲህ ይህ ታላቅ ሕዝብ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት
የተጎናጸፈውን በክልል የመደራጀት ጥያቄ በሽግግር ወቅት
በክልል ዘጠኝ ከተደራጀበት ወደ ደቡብ ክልል ተጨፍልቆ
እንዲዋቀር ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ እራስን በራስ የማስተዳደር
ጥያቄ ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን በተለይ በ1992 ዓ.ም በሚሊዮኖች
የሚቆጠሩ የብሔሩ ተወላጆች በጥቂት የፓለቲካ ሊህቃን
የህዝቡን ማንነት የሚጨፈልቅ ሰዉ ሰራሽ "ወጋጎዳ" የተባለ
ቋንቋ በሥርዓተ ትምህርት ቀርጸው በማምጣታቸዉ አደባባይ
ወጥቶ ተቃዉሞ በማድረግ ህዝባዊ ትግል በማድረግ
መስዋዕትነት ከፍሎ ህገ መንግስቱ እንዲከበር ፋና ወጊ ሚና
በመጫወት ማንነቱን እና ህልውናውን ማስጠበቅ የቻለ እና
አሁን የሚገኝበትን የዞን መዋቅር ያገኘ እና የአጎራባች ህዝቦች
መብት እንዲከበር ታግሏል:: እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ
ለአንድ መቶ ሃያ አምስት ዓመታት የቆየ ሲሆን ተጨፍልቆ
በቆየበት ጊዜ በህገ ወጦች እና ስግብግቦች አማካኝነት
በማንነቱ፣ በታሪኩ፣ በባህሉ እና በህልዉናው ላይ የደረሰበትን
እና እየደረሰ ያለውን መዋቅራዊ በደል እና ጭቆና ለማስቀረት
ሰላማዊ ትግል ሲያደርግ ቆይቷል:: የዎላይታ ህዝብ ህግ
መንግስት ያጎናጸፈውን እራስን በራስ የማስተዳደር እና የራስን
ክልል የመመስረት መብቱን መሰረት በማድረግ ከቀበሌ ምክር
ቤት እስከ ዞን ምክር ቤት ድረስ በሙሉ ድምጽ አፅድቆ ህዝበ
ዉሳኔ እንዲመቻች ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ለክልሉ ም/
ቤት ልኮ ምላሽ እየተጠባበቀ ባለበት ባሁኑ ሰዓት የደኢህዴን
ማዕከላዊ ኮሚቴ የዎላይታ ህዝብ እና ሌሎች የክልሉ ህዝቦች
ባቀረቡት በክልል የመደራጀት ጥያቄዎች አስመልክቶ ውሳኔ
ማሳለፉን ሐምሌ 08 ቀን 2011 ዓ.ም ባወጣዉ መግለጫ ይፋ
አድርጓል፡፡
ይሁን እንጂ ውሳኔዉ የተድበሰበሰ ከመሆኑ ባሻገር የኢትዮጵያ
ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በህገመንግስቱ የተረጋገጡ ራስን
በራስ የማስተዳዳር መብቶችን እና የብሄሮችን ዕኩልነት
በአደባባይ የጣሰ መሆኑን በመገምገም የዎላይታ ዬላጋ
የሚከተለዉን ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥቷል፡፡
1. ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የወላይታን ሕዝብ ጥያቄ
አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔም ሆነ አስጠንችያለሁ ያለውን
ሳይንሳዊ ያልሆነ፣ የፐለቲካ ጠልቃ ገቢነት ያለው፣ አድሏዊና
በጭፍን ጥላቻ የተነዳ ጥናት አጥብቀን የሚንቃወም መሆናችን
ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ይህንን ስንል እርሶ የመንግሥት ሕግ
አስፈጻሚ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪና የአገሪቱ መሪ ድርጅት
ልቀመንበር በመሆንዎ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትንም ሆነ
አባል ድርጅቶችን በመጠቀም የግል ጥቅማቸውንና ፍለጎታቸውን
መሰረት ባደረገ መልኩ በሕዝዘብ ሕልውና ላይ አደጋ
የሚያስከትል የፖለቲካ ጨዋታ እየተጫወቱ ያሉ አካላትን አደብ
ሊያስገዙልንና ፍትሐዊና ሕገመንግሥታዊ አካሄድ እውን
እንዲሆን የበኩልዎችን ሚና ይጫወታሉ የሚል እምነት ስላለን
ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከወላይታ ሕዝብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ
ሕዝባችንን በአካል ተገኝተው ለማነጋገር መወሰንዎን ስንሰማ
ትልቅ ደስታ ተሰምቶናል፣ ጥያቄው እንዲመለስ አዎንታዊ ሚና
ይጫወታሉ የሚል ተስፋንም ጥለንቦታል፡፡ ስለሆነም ባለ 6ሺህ
ዕድሜ ታሪክ ባለቤት፣ የቀደምት ነገስታት መፍለቂያና
በኢትዮጵያዊ አንዲነት ላይ ጉልህ አሻራ ወደላው ወደ ታላቋ
ወላይታ እንኳን ደህና መጡ ለማለት እንወዳለን፡፡ ሀሹ ሳሮ ዬታ!
2. የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫዉ ሁሉም ብሔር፣
ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የየራሳቸዉን ክልል የመመስረት ህገ
መንግስታዊ መብት ያላቸዉ መሆኑን የሚገነዘብ እንደሆነ የገለፀ
ቢሆንም በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ያለዉን ዕኩልነት
በሚጣረስ መልክ የዎላይታን ብሔር ጥያቄ በሴራ እና በንቀት
በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 8፣ 25 ፣39፣ 46 እና 47 ላይ
ለብሔር ብሔረሰቦች የተሰጡ መብቶችን የሚጣረስ መግለጫ
ያወጣ በመሆኑ ይህ ኢ-ህገ መንግስታዊ እና አምባገነናዊ ውሳኔ
ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አጥብቀን እንገልጻለን፤
3. የዎላይታ ህዝብ የራስን ክልል የመመስረት ህገ መንግስታዊ
መብትን መሰረት በማድረግ ከቀበሌ ምክር ቤት እስከ ዞን ምክር
ቤት ድረስ በሙሉ ድምጽ አፅድቆ ህዝበ ውሳኔ እንዲዘጋጅ
ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ወደክልሉ ም/ቤት የላከውን ውሳኔ
ለምክር ቤት እንዳይቀርብ ያለ ህጋዊ ሥልጣን ኢ-ህገ
መንግስታዊ በሆነ መንገድ በማገድ ላለፉት 8 ወራት 'እኔ
አውቅልሃለሁ' በሚል ያረጀ የፖለትካ ድስኩር ማዘግየቱ ከአንድ
የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ተወካይ ነኝ ከሚል የፖለቲካ
ድርጅት የማይጠበቅ ኢ-ዴሞክራሲያዊ፣ ኢ-ፍትሐዊ እና ኢ-
ሞራላዊ ድርጊት ስለሆነ የዎላይታ ብሔር ጥያቄ በአስቸኳይ
ለክልሉ ም/ቤት ቀርቦ ህዝበ ውሳኔ እንዲያደራጅ ለኢትዮጵያ
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንድያስተላልፍ እየጠየቅን ይህ የማይሆን
ከሆነ በህገመንግስቱ አንቀፅ 47 የተቀመጠው የአንድ ዓመት
ጊዜ ገደብ እንደተጠናቀቀ የዎላይታ ብሄር ም/ቤት ውሳኔውን
በራሱ ለማስፈጽም አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ አጥብቀን
እናሳስባለን፤
4. ዉድ የሀገራችን ህዝቦች የዎላይታ ሕዝብ በግንቦት ወር፣
2011 ዓ.ም ባደረገዉ ሠላማዊ ሰልፍ በሀገርቷ እየታየ ያለውን
ለውጥ በሚሊዮኖች አደባባይ ወጥቶ መደገፉን የገለፀ ቢሆንም
በህገ መንግስቱ ለሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ዕኩል ጥበቃ
የተደረገውን መብት ሀገ መንግስቱን በመጣስ የደኢህዴን
ማዕከላዊ ኮሚቴ ለአንዱ ብሔረ ጥያቄ በህገ መንግስቱ
መሰረት ህዝበ ውሳኔ ይደረግ፤ ዎላይታ ደግሞ ከሌሎች ጋር
ተጨፍሎቆ ማንነቱን በማይገልፀው ደቡብ ክልል ይቀጥል
በማለት መወሰኑ በአንድ ሀገር ዉስጥ ሁለት ዓይነት ዜግነት ያለ
በማስመሰል የዎላይታ ህዝብ በለውጡ ላይ የሰነቀውን ተስፋ
የሚያስቆርጥ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም የደኢህዴን ማዕከላዊ
ኮሚቴ ከህግ አግባብ ውጭ የወሰነዉ ውሳኔ በክልሉ ም/ቤት
እና በፌዴራል መንግስት ተቀባይነት እንዳይኖረው እና ውድቅ
እንዲደረግ እንጠይቃለን፤
5. ውድ በዎላይታ የምትኖሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆች:
የዎላይታ ብሄር ህገ መንግስታዊ መብቱን በብሔሩ ም/ቤት
በሙሉ ድምጽ ወስኖ በሰላማዊ መንገድ ህዝበ ዉሳኔ
እንዲመቻች ለክልሉ ም/ቤት ጥያቄ የላከ ቢሆንም በመዘገየቱ
መነሻ ግንቦት 9 ቀን 2011 ዓ.ም ሁላችሁም ሐይማኖትና
ብሔር ሳትለዩ በነቂስ ወጥታችሁ በታላቁ ሰላማዊ ሰልፍ
በአንድነት የደገፉችሁትን እዉቅና እየሰጠን ከግብ እንዲደረስ
አጋሪነታችሁን አጠናክራችሁ እንዲትቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
6. ውድ የኢህአደግ ግንባር ድርጅቶች: የዎላይታ ብሔር
የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ለብሔረ ብሔረሰቦች በዕኩልነት
ያጎናጸፈውን ህገ መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ታሪካዊ
ማንነቱን እና ህልናዉን ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ
በብሔሩ ም/ቤት በሙሉ ድምጽ ወስኖ በሰላማዊ መንገድ ህዝበ
ዉሳኔ እንዲመቻች ለክልሉ ም/ቤት ጥያቄ የላከዉ እና
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በአንድነት አደባባይ ወጥተዉ የደገፉት
ለህገ መንግስታዊ መብት እና ለህግ የበላይነት የተደረገ
ዴሞክራሲያዊ ትግል መሆኑን በመገንዘብ በኢህአዴግ ድርጅታዊ
መድረኮች የደኢህዴንን ፀረ ህገ መንግስት እና ኢ-ሞራላዊ
የሆነ ዉሳኔ እዉቅና ባለመስጠት እና በማዉገዝ እንድታርሙ
እየጠየቅን የዎላይታ ብሔር ጥያቄ ከግብ እንዲደርስ
አጋሪነታችሁን ዛሬም አጠናክራችሁ እንዲትቀጥሉ ጥሪ
እናቀርባለን፡፡
7. ዉድ የአጎራባች ህዝቦች: የዎላይታ ብሔር የኢፌዴሪ ህገ
መንግስት ለብሔረ ብሔረሰቦች በዕኩልነት ያጎናጸፈው ህገ
መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ታሪካዊ ማንነቱን እና ህልዉናዉን
ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ በክልልነት ለመዋቀር
የሚያደርገዉ ትግል በሀገራችን የብሔር ብሔረሰቦች ህገ
መንግስታዊ መብት እንዲከበርና የህግ የበላይነት እንዲሰፍን
የሚደረግ ዴሞክራሲያዊ ትግል መሆኑን በመገንዘብ
የደኢህዴንን ፀረ ህገ መንግስታዊ ውሳኔ እዉቅና ባለመስጠት
እና በማዉገዝ ከጎናችን እንድትሆኑ እንጠይቃለን፡፡
8. ውድ የአጎራባች ዞን ሕዝቦች፣
ሁላችሁም እንደሚታወቁት በርካታ አንድ የሚያደርጉን የጋራ
እሴቶች እንዳሉን ሁሉ የየራሳችሁ ማንነት፣ ቋንቋና ባህል ባለቤት
እንደሆናችሁ የዎላይታ ዬላጋ ይገነዘባል፡፡ በዚህም መሰረት
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የእራሳችሁን ዕድል በራሳቸው
የመወሰን ሕገመንግስታዊ መብታችሁን በመጠቀም
በክልልነትም ሆነ ከዚያ በመለስ ለመደራጀት በሚታደርጉት
ሰላማዊ ትግል የዎላይታ ዬላጋ ከጎናችሁ የሚቆም መሆኑን
ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ የዎላይታ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ
የመወሰን መብትን ተጠቅሞ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ካነሳበት
1985 ዓ.ም ጀምሮ እሰካሁን ሲታገልና በርካታ መስዋዕትነቶችን
ሲከፍል መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የዎላይታ ሕዝብ የራሱን መብት
ለማስከበር እንደሚታገል ሁሉ የአጎራባች ዞኖች ሕዝቦችንም
መብት የሚያከብር፣ ጥቅማቸውን የሚጎዳና መብታቸውን
የሚነካ ማናቸውንም አካሄድም ሆነ አቋም አምርሮ የሚጠየፍና
የሚቃም መሆኑን በዚህ አጋጣሚ የዎላይታ ዬላጋ ለመግለጽ
ይፈልጋል፡፡ የዎላይታ ሕዝብ በክልል ለመደራጀት ያቀረበውን
ፍጹን ሕገመንግሥታዊና ሰላማዊ ጥያቄ በደኢህዴን ማን
አለብኝነት ሲታፈን መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የዎላይታ
ሕዝብ ጥያቄው እስክመለስ ፍጹም ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ
ስለሚቀጥል ከጎናችን እንዲትቆሙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
9. በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚትኖሩ
ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትይጵያ በሙሉ፣
እኛ የዎላይታ ዬላጋዎች ለዎላይታ ብቻ ሳይሆን ለመላ ሰው ዘር
ሁሉ ፍትህ፣ እኩልነትና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር
የሚንታገል ሕዝባዊ ባህርይ የተላበስን የዎላይታ ብሔር አባል
የሆንን ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያዊ አንድነትም
ሆነ በአገራዊ ልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ተደማሪ
አስተዋጽኦ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እንዲረጋገጥ በሚደረገው
ሰላማዊ ትግል ከሁሉም ሰላማዊ የሚያደርግ ኢትዮጵያ ጋር
አብረን የሚንታገል መሆናችን ለመግለጽ እንወደዳለን፡፡ እኛ
የዎላይታ ዬላጋዎች የክልል ጥያቄ የሚናነሳቸው የዎላይታ ሕዝብ
ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምንጩ ፓለቲካዊ በመሆኑ በሕዝባችን ላይ
የተጋረጠብን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን
ለመቅረፍ እንዲቻል እንጂ በኢትዮጵያዊ አንዲነት ቅንጣት ያህል
ጥርጣሬ አይግባችሁ፡፡ ዎላይታ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ለአገሩ ሟች
ነው፡፡ የዎላይታን ጥያቄ መመለስና ችግሩን መፍታት
የኢትይጵያን ችግር መፍታት ነው፡፡
10. ዉድ የዎላይታ ዬላጋ አባላት፣ የዎላይታ ብሔር ተወላጅ
የሆናችሁ ዲያስፖራዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣
የሐይማኖት አባቶች ፣ነጋዴዎች ፣አርሶ አደሮች፣ የመንግስት
ሠራተኞች ፣ የግል ባለሁብቶች ሆይ ከቀበሌ ም/ቤት እስከ ዞን
ም/ቤት ድረስ በጥሞና መክራችሁ እና በታላቁ ሰላማዊ ሰልፍ
በሚሊዮኖች አደባባይ ወጥታችሁ ህልናዉችሁን ለማስጠበቅ
በሙሉ ድምጽ ይዉንታ የሰጣችሁን ህገ መንግስታዊ ጥያቄ
በደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ኢ-ህገ መንግስታዊ በሆነ አሠራር
መሰናክል የገጠመዉ መሆኑን ተገንዝባችሁ ይህንን ለዕኩልነት፣

ለፍትህ፣ ለህገ መንግስታዊ መብት፣ እና ለህግ የበላይነት

የሚታደረጉትን ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ትግል ከማንኛዉም
ጊዜ በተሻለ አንድነት እና ህብረት ጥያቄዉ እስኪመለስ ድረስ
አጠናክራችሁ እንዲትቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
11. በመጨረኛም ትግላችን ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና
ሕገመንግስታዊ መሆኑ ታውቆ ይሄ እውነታ ካልገባቸው አንዳንድ
አካላት በተለይ የደኢህዴን አመራሮች ነን ከሚሉ አካላት
በሕዝባችንና ሕዝባችን እንደ አይኑ ብለን በሚያያቸው የለውጥ
አመራሮቻችን ላይ የሚካሂዱት በጭፍን ጥላቻ የተሞላ ትንኮሳና
ኢ-ሕገመንግስታዊ የሆነ አካሄድን የዎላይታ ዬላጋ አጥብቆ
ይቃወማል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የደኢህዴን አመራሮች ለዎላይታ
ሕዝብ እያሳዩት ያለው ንቀትና እብሪት የተሞላበት ዛቻ ወቅቱን
ካለመገናዘብ፣ የዎላይታን ሕዝብ በአግባቡ ካለመረዳት
እንዲሁም ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመራር ቁመና፣
ብስለት፣ጥበብ፣ ክህሎትና አቅም ካለመላበስ የመነጨ
እንደሆነም ዬላጋ ያምናል፡፡ የዎላይታ ዬላጋ በዛቻ፣
በማስጠንቀቂያ፣ በኢ-ህገመንግሥታዊ እርምጃና ስነ ልቦናዊ
ጫና ለመፍጠር በሚደረግ በማንኛውም ጸረ-ዎላይታ ሕዝብ
ጥያቄ በሆነ አካሄድ የሚቆም ትግል አለመኖሩን ይሄንን
የሚያካሂዱ አካላት እንዲገነዘቡ እየጠየቀ ይህ ሳይሆን ከቀረ
ግን መከፈል የማይገባ ዋጋ የሚያስከፍል የተሳሳተ አካሄድ
መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ሰላማዊ ትግሉ የሕዝባችን ጥያቄ እስክመለስ
ድረስ ለአፍታም የማይቆም መሆኑን በድጋሚ ለማረጋገጥ
እንወዳለን፡፡
አንድ ዬላጋ ለሁሉ ዬላጋ፣ ሁሉ ዬላጋ ለአንድ ዬላጋ፡
አንድ ዎላይታ ለሁሉ ዎላይታ፣ ሁሉ ዎላይታ ለአንድ ዎላይታ፡፡
የዎላይታ ብሔራዊ ክልል፡፡
እግዝአብሔር ዎላይታን ይባርክ!
እግዚአብሔር ኢትይጵያን ይባርክ!
የዎላይታ ዬላጋ ምክር ቤት
ሐምሌ 19፣ ቀን 2011 ዓ/ም
              ዎላይታ ሶዶ
             

Wednesday, July 24

እውነት/FACT: በአይሁዶች መርዘኛ ጥርስ የገባች ሀገር ኢትዮጵያ! ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋ...

እውነት/FACT: በአይሁዶች መርዘኛ ጥርስ የገባች ሀገር ኢትዮጵያ! ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋ...: “ ለይሁዳ ወልዱ ወለ ውሉደ ውሉዱ የደምሰስ ( የይሁዳ ልጅና የልጆቹ ልጆች ይደምሰሱ )” ትላለች የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዐቢይ ጾም የመጨረሻ ሳምንት በሰሙነ ሕማማት የጾም ...

Tuesday, July 23

Home | Dessie Dalga: ወላይተኛ ቋንቋ እና ወላይታ /በኢትዮጵያና በደቡብ

Home | Dessie Dalga: ወላይተኛ ቋንቋ እና ወላይታ /በኢትዮጵያና በደቡብ: '''➊✍ወላይትኛ''' በ[[ኢትዮጵያ]] በተጠቃሚ ብዛት በ4ኛነት የሚመደብና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሌሎቹ ተቀራራቢ ቋንቋዎች ምንጭ ...

Home | Dessie Dalga: ትልቅ የነበሪን/ወላይታ ፦ማስታዎሻነቱ ሰኔ 16/2010 በብሔረ ተኮር ጭፍጨፋ አ...

Home | Dessie Dalga: ትልቅ የነበሪን/ወላይታ ፦ማስታዎሻነቱ ሰኔ 16/2010 በብሔረ ተኮር ጭፍጨፋ አ...: Dessie D Ethiopian ☞ ትልቅ የነበሪን☜፦ ከኪንዶ ዲዳዬ እስከ ዱጉና ፋንጎ ወሰን ያስፋፋን፣ ከኦሞ ተነስተን ሓማሳና ብላቴን ያካለልን፣ ከቢቶ እስከ ጦና ጋጋ 50 ነገሥታት የነበረን ። ከቄስ ትም/ቤት ወደ ሊ...

ZELALEM TILAHUN (የ እናቱ ልጅ): ›››የሐበሻ ጀብዶ›››የኢትዮጵያውን የነፃነት ተጋድሎ›››

ZELALEM TILAHUN (የ እናቱ ልጅ): ›››የሐበሻ ጀብዶ›››የኢትዮጵያውን የነፃነት ተጋድሎ›››:                                          ለፒዲኤፍ ይህንን ይጫኑ ኢትዮጵያዊ ነህ? ሐበሻ ነህ? ሐበሻ ከሆንክ መጀመሪያ የሐበሻ ጀብዶንና ቀይ አንበሳን አንብብ፡፡ የቅድመ አያትህ፣ ...

Featured Posts

“ግብፅ ግድቡን የሚመታ ራፋል የተባለ የጦር አውሮፕላን ገዝታ ነበር” የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም የተወለዱት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ የጁ ወረዳ በምትገኝ አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው። የልጅነት ጊዚያቸው...

Blogger