Thursday, February 28

Popular posts of the this Blog


(ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)
አንድ ሞኝ አሽከር የነበረው ሰው ነበር አሉ፡፡ ይኼ አሽከር አድርግ
የተባለውን ካልሆነ በቀር አስቦ፣ አውጥቶ እና አውርዶ፣ ብሎም
አመዛዝኖ የሚሠራው ሥራ አልነበረም፡፡ምን ጊዜም
የሚጠብቀው የጌታውን ትእዛዝ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ትክክል ነገር
ማለት ጌታው ያዘዘው ሲሆን፣ ስሕተት ማለት ደግሞ እርሱ
ያልነገረው ነገር ማለት ነው፡፡ ዓላማው ጥሩ ነገር መሥራት
ወይንም አዲስ ነገር መሥራት ሳይሆን ጌታውን ማስደሰት ብቻ
ነበር፡፡ ጌታው ከሳቀ ይስቃል፣ ካለቀሰ ያለቅሳል፣ ከተደሰተ
ይደሰታል፣ ካዘነም ያዝናል፡፡የወደደውን ይወድዳል የጠላው
ይጠላል፡፡ ለርሱ የመደሰቱንም ሆነ የማዘኑን፣ የመሳቁንም ሆነ
የማልቀሱን ምክንያት ማወቅ አይጠበቅበትም፡፡ ዋናው ነገር
ጌታው መሳቁ ወይንም ማልቀሱ ነው፡፡ አንዳንዴ ሰዎች
የሳቀበትን ምክንያት ሲጠይቁት «ጌታው ሳቁኮ! አላያችሁም?»
ይላል፡፡ በዚህም የተነሳ ሰዎች «እንዳሉት»ብለው ይጠሩት
ነበር፡፡
.
አንድ ቀን ጌታው እና እንዳሉት ወደ መንገድ ወጡ፡፡ እርሱ
በእግሩ ከኋላ እየተከተለ፤ ጌታው ደግሞ በፈረስ ከፊት
እየበረሩ፡፡ መንገድ ላይ ጌታው የገንዘብ ቦርሳቸውን ጣሉት፡፡
እንዳለውም ቦርሳውን አልፎት ሄደ፡፡ጌታው ያሰቡበት ከተማ
ገብተው ኪሳቸውን እስኪቀደድ ቢበረብሩ ቦርሳቸውን ሊያገኙት
አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም ወደ እንዳሉት ተጠጉና «የገንዘብ
ቦርሳ አላየህም» አሉት፡፡ እንዳሉት «አይቻለሁ፣ መንገድ ላይ
ጥለውታል» አላቸው፡፡ ጌታው ደንግጠው እና ተናድደው «ታድያ
ለምን አንሥተህ አልሰጠኸኝም» አሉት፡፡ እንዳሉት ደንግጦ
አሰበ፣ አሰበ፣ አሰበ፡፡ ግን የተሰጠው መመርያ አልነበረም፡፡
ተከተለኝ ከማለት በቀር የነገሩት ነገር አልነበረም፡፡ «እንዴ
እርስዎ የገንዘብ ቦርሳዬ ሲወድቅ አንሥተህ እንድትሰጠኝ መች
አሉኝ» አላቸው፡፡ እርሳቸውም «በል ከዛሬ ጀምሮ እኔ በፈረስ
ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካየህ ሰብስበህ እንድትሰጠኝ» አሉት፡፡
ከእሺ በቀር ሌላ የማያውቀው እንዳሉት በጸጋ ተቀበለ፡፡
.
በቀጣዩ ጊዜ ጌታውን ተከትሎ መንገድ ጀመረ፡፡ መመርያው
በልቡ ነበር፡፡የሚያሳስበው የተነገረው ነገር ነው፡፡ በልቡ
ውስጥም ከተነገረው ነገር በቀር ምንም ሌላ ነገር አልነበረም፡፡
የርሱ ልብ አዲስ ነገር አያመነጭም፤ አዲስ ነገር ማመንጨት
የሚችሉት የርሱ ጌታ ብቻ ናቸው፡፡ የርሱ ሥራ ያለ ጥርጥር
ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት ማለት ብቻ ነው፡፡ ለምን? ማለት
አያውቅም፡፡ ለምን? ማለት ከጀመረማ አሽከር አይሆንማ፡፡
አሽከር ደግሞ ይጠይቃል የታዘዘው ትእዛዝ ብቻ ነበር ትዝ
የሚለው፡፡ «እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካገኘህ ሰብስበህ
እንድትሰጠኝ» የሚለው፡፡ ይህ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ አንዳች
ነገር እንዲወድቅ ተመኘ፡፡ ያለበለዚያማ ትእዛዝ ፈጻሚ ላይሆን
ነው፡፡ የሚወድቅ ነገር ከሌለማ እርሱ የወደቀን ሰብሳቢ መሆኑ
እንዴት ይታወቃል? ስለዚህ ለመሰብሰብ ሲባል ብቻ መጣል
አለበት፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አንዳች ነገር መውደቅ ጀመረ፡፡
እርሱም እያነሣ በቀረጢት ከተተ፡፡ ሲወድቅ ሲያነሣ፣ ሲወድቅ
ሲያነሣ፣ ሲወድቅ ሲያነሣ በመጨረሻ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡
ጌታውም «እህሳ፣ ዛሬስ የወደቀ ነገር የለም?» አሉት፡፡ «አለ
እንጂ» አላቸው፡፡ ደንግጠው ኪሳቸውን ዳበሱት፡፡ ቦርሳቸው ከነ
ገንዘቡ እንዳለ ነው፡፡
.
«ምንድን ነው የወደቀው?» አሉት ጌታው፡፡ እንዳሉት ግን
ቀረጢቱን ይዞ መጣ፡፡ ሲከፍተው የፈረሱ ፋንድያ ነበር፡፡ «ይህንን
ምን ሊጠቅምህ ሰበሰብከው?» አሉት ጌታው፡፡
«እኔ በፈረስ ስሄድ የሚወድቅ ነገር ካገኘህ ሰብስብ ብለውኛላ»
አላቸው፡፡ እውነቱን ነው፡፡ አሽከር አንድ ነገር ይጠቅማል፣
አይጠቅምም፤ ያስፈልጋል፣ አያስፈልግም ብሎ እንዲወስን ማን
ፈቀደለት? አሽከር ማለት የታዘዘውን ብቻ የሚፈጽም ማለት
ነው፡፡ አሽከር ከአንገት በታች እንጂ ከአንገት በላይ አለው እንዴ?
«በል» አሉት ጌታው፡፡ «ከዛሬ ጀምሮ የምታነሣው ቦርሳዬ፣
ካባዬ፣ ባርኔጣዬ፣ ጅራፌ፣ ገንዘቤ፣ እንዲሁም ከፈረስ ዕቃዬ
አንዱ ነገር ከወደቀ ብቻ ነው»፡፡ እንዳሉት በፈገግታ ተቀበለ፡፡
ግን ፈራ፡፡ ይህንን ዝርዝር ቢረሳውስ፡፡ ቁጭ ብሎ በአንድ
ወረቀት ላይ ጻፈው፡፡ መጻፍ ብቻ አይደለም እንደ ውዳሴ
ማርያም ደጋገመው፡፡
.
ለሦስተኛ ጊዜ መንገድ ተጓዙ፡፡ እንዳሉት እና ጌታው፡፡በሄደበት
መንገድ ሁሉ የሚጓዝበትን አካባቢ፣ ዛፎቹን እና እንስሳቱን፣
መንደሩን እና መስኩን አያይም፡፡ እየደጋገመ የሚያየው ዝርዝሩን
ነው፡፡ አንዴ ዝርዝሩን፣ አንዴም መንገዱን ያያል፡፡ ከዝርዝሩ
መካከል መሬት የወደቀ እንዳለ ብሎ፡፡ እርሱም ዝርዝሩን እንዳየ
ጌታውም እንደሸመጠጡ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡ «እህሳ ዛሬስ
የወደቀ ነገር አለ?» አሉት፡፡ «የለም፤ ከዝርዝሩ ውስጥ የወደቀ
ነገር የለም» አላቸው፡፡ ለእርሱ ዋናው የሚጠቅም ነገር
ወድቋል? የሚለው አይደለም፤ ከዝርዝሩ መካከል፤ ከታዘዘው
መካከል ወድቋል ወይ? የሚለው ነው፡፡ ከዝርዝሩ ውጭ ምን
ነገር አለ? ማንኛውም ነገር ያለው በዝርዝሩ ውስጥ ብቻ ነው፡፡
ከዝርዝሩ ውጭ ያለ ነገር አንድም እንዳለ አይቆጠርም፤
ያለበለዚያም የማይጠቅም ነገር ነው፡፡ ዋናው ዝርዝሩ ነው፡፡
ለርሱ ዝርዝሩ ቁጥሩ ከወንጌል፣ አንዳንዴም ከወንጌል በላይ
ነው፡፡ ደስ አለው፡፡ ከዝርዝሩ መካከል የነጠበ ነገር የለምና፡፡
.
ከብዙ ጊዜ በኋላ እንዳሉት እና ጌታው ለአራተኛው ጉዟቸው
ተነሡ፡፡ እርሳቸውም ፈረሳቸውን እርሱም ዝርዝሩን አዘጋጁ፡፡
ሄዱ፡፡ ሸመጠጡ፡፡ እርሳቸው ፊት ፊታቸውን፣ እርሱም ዝርዝሩን
እያዩ፡፡ ዋናው ዝርዝሩ ነው፡፡ ሲሄዱ፣ ሲሄዱ፣ ሲሄዱ መንገድ ላይ
ፈረሱ አደናቀፈውና ጌታውን ይዟቸው ወደቀ፡፡ፈረሱም የሲቃ
ድምጽ አሰማ፡፡ ጌታውም ጮኹ፡፡ «አንሣኝ አንሣኝ» እያሉ ጮኹ
ጌታው፡፡ እንዳሉት ዝቅ ብሎ በእጁ ያለውን ዝርዝር አየ፡፡ ጌታው
ሲወድቁ እንዲያነሣ የሚያዝ በዝርዝሩ ውስጥ የለም፡፡
« #አላነሣዎትም » አላቸው፡፡ «ለምን ለምን፤ ኧረ ተላላጥኩልህ
አንሣኝ» አሉት በልመናም በትእዛዝም፡፡ «የለም ጌታው በዝርዝሩ
ውስጥ እርስዎ የሉም» በመካከል ፈረሱ ተነሣ፡፡ ጌታው ግን
ሰውነታቸው ተላልጦ እየደማ እዚያው ያቃስቱ ጀመር፡፡ ፈረሱ
መንገዱን ይዞ ሸመጠጠ፡፡ ጌታው እጃቸውን እያርገበገቡ
«እባክህ ስለ ፈጠረህ አምላክ አንሣኝ» እያሉ እንዳሉትን
ለመኑት፡፡ እርሳቸው ያንን ዝርዘር ሲሰጡት ቃላቸውን
ለማስጠበቅ እና ከቃላቸው እንዳ ይወጣ እንጂ እርሳቸው
ሊወድቁ እንደሚችሉ መች ገመቱ፡፡ ደግሞስ ጌታ እወድቃለሁ
ብሎ እንዴት ይገምታል፡፡ አሁንም እጃቸውን እያርገበገቡ
ለመኑት «አንሣኝ አንሣኝ እባክህ» እንዳሉት ግን ፈረሱን ተከትሎ
አሁንም ዝርዝሩን እያየ ትቷቸው ሮጠ፡፡ ብቻውን «እንዴ እዚህ
ዝርዝር ውስጥ የሌሉትን እንዴት ብዬ ላንሣቸው፡፡በኋላ ደግሞ
ከዝርዝሩ ውጭ አነሣህ ብለው ራሳቸው ቢቆጡኝስ፡፡ እኔ ካዘዙኝ
ውጭ ሠርቼ ዐውቃለሁ? አሁን ማንን ክፉ ለማድረግ ነው» እያለ
ያጉረመርም ነበር፡፡

x

Saturday, February 16

የብሔር ተዋጽዖ/በዳንኤል ክብረት ዕይታ

ለብሔር ብሔረሰቦች በዓል የመጡ ሰዎች በጀልባ
እንዲንሸራሸሩ ተባለ፡፡ ከየብሔረሰቡ ሰው ወደ ጀልባዋ ገባ፡፡
ጀልባዋም ቀስ እያለች መንሳፈፍ ጀመረች፡፡ ተንሸራሻሪዎቹም
ብሔር ብሔረሰቦችን እያመሰገኑ በስማቸው መንሸራሸር
ቀጠሉ፡፡ የሽርሽሩ ዳርቻ ደርሰው ሲመለሱ ግን ከባድ ማዕበል
ተነሣ፡፡ ጀልባዋም የግልንቢጥ ትደንስ ጀመር፡፡ ግማሹ
ይጸልያል፣ ግማሹ ይሳላል፣ ግማሹ ይዘላል፤ ሌላው ጥግ
ይፈልጋል..
የጀልባዋ ነጅ ያሰማውን የድረሱልኝ ጩኸት ሰምተው የመጡት
የከተማው ሰዎች ሐይቁ ዳር ቆመው ይጨቃጨቃሉ፡፡
‹እንዴት አድገን እንርዳቸው?› አለ አንዱ፡፡
‹ሁሉንም ብሔር በሚያመጣጥን መንገድ ነው መርዳት
ያለብን› አለ ሌላው
‹ሞት ደግሞ ምን ተዋጽዖ አለው› አሉ አንድ አዛውንት
‹ኖ ኖ ስናወጣቸው ከአንድ ብሔረሰብ እንዳይበዛ፤ ከሁሉም
እኩል እኩል ሰው ነው ማዳን ያለብን›
‹ቆይ ከየብሔረሰቡ ስንት ስንት ሰው ነው የገባው›
‹አናውቅም፤ ብቻ አወጣጣችን ፍታዊ መሆን አለበት›
‹አሁን እኛ ቶሎ ደረስን ተረባርበን ማውጣት እንጂ፣
ከየብሔረሰቡ ሁለት ሁለት ሰው ኑ፤ ልንል ነው? አሁን በነፍስ
የተያዘ ሰው መዳኑን እንጂ ብሔረሰቡን ያስብልሃል? ለመሆኑ
ሲሰጥሙ ከየብሔረሰቡ ተመጣጥነው ነው የሚሰጥሙት?›
አሉ አዛውንቱ ገርሟቸው፡፡
‹አንድ ማስተካከያ አለ› አለ አንድ ጎልማሳ፡፡ ሁሉም ዞር
ብለው አዩት፡፡
‹የእንትን ብሔረሰብ እኛን አያገባንም፡፡ ሲጨቁን፣ ሲመዘብር፣
ሲዘርፍ የኖረ ነው፤ ጦሱ ያውጣው፤ እነርሱን ማውጣት
የለብንም›
‹እንደዚያማ ከሆነ፣ ቅድሚያ ማግኘት ያለበት የኛ ብሔረሰብ
ነው፡፡ ታግለን፣ ለፍተን፣ ሞተን እንዲህ በጀልባ እንዲዝናኑ
ያደረግናቸውኮ እኛ ነን›
‹እሱን እንኳን ተዉት፤ እኛ በወርዳችንና በቁመናችን ልክ ነው
ማግኘት ያለብን፡፡ ከሞት ከሚተርፉት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ
የእኛ እንዲሆኑ እንፈልጋለን፡፡›
የሚሰጥሙትን ሰዎች ለማዳን የመጡት ሰዎች
ይጨቃጨቃሉ፡፡
የጀልባዋ ሩብ ወደ ሐይቁ ገባ፡፡
‹ጎበዝ፤ እናንተ ስትጨቃጨቁ ሰዎቹኮ እየሰመጡ ነው፡፡ ለምን
ተረባርበን ሁሉንም አናወጣቸውም› አለ አንድ ልጅ እግር፡፡
‹የብሔር ፖለቲካ ያልገባህ ጩጬ ነህ› አለው ጎልማሳው፡፡
‹መጀመሪያኮ ሰው ሲኖር ነው ብሔር የሚኖረው፤ ሰው እየሞተ
ብሔር ምንድን ነው› አለው ልጅ እግሩ፡፡
‹አልገባህም ያልኩህኮ ይኼንን ነው፡፡ ሰው ይሞታል፤ ብሔር
ይቀጥላል›
‹ቆይ አሁን እዚያ ጀልባ ውስጥ እየሰመጡ ያሉት ብሔሮች
ናቸው ወይስ ሰዎች?›
‹ብሔር ብሔረሰቦችን ወክለው ነው የሚሰምጡት› አለ
ጎልማሳው፡፡
‹የትኛው የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ሄደው ነው
ብሔረሰቦች እነዚህን ሰዎች የወከሉት›
‹እይውልህ ጅሉ፤ ሰዎቹ እስከሚሞቱ ብሔር ይወክላሉ፤ ሲሞቱ
ግን - ሟቾቹ የትኛውንም ብሔር አይወክሉም- የሚል
መግለጫ ይወጣል› አለው ጎልማሳው፡፡
‹ኧረ ሰዎቹ ከመስጠማቸው በፊት እናውጣቸው› አለ ልጅ
እግሩ በጩኸት፡፡
‹አውጭዎቹም ብንሆን ከሁሉም ብሔረሰቦች የተውጣጣን
መሆን አለብን› አለና ጎልማሳው ሰዎችን መምረጥ ጀመረ፡፡
አንድ ዐሥር ብሔረሰቦችን ‹የሚወክሉ› አውጭዎች
አልተገኙም፡፡
‹ወደየ ብሔረሰቡ እንሂድና ከየብሔረሰቡ ሰው መርጠን
እናምጣ› አለ ጎልማሳው፡፡
የጀልባዋ ግማሽ ሰመጠ፡፡
‹ሰዎቹኮ እየሰመጡ እንጂ እየተዝናኑ አይደሉም፤ ለምን እኛ
ገብተን ሁሉን አናወጣቸውም› አለ ልጅ እግሩ፡፡
‹ኖ ኖ ይሄማ እኔ ዐውቅልሃለሁ ማለት ነው፡፡ ብሔር
ብሔረሰቦች ራሳቸውን የማዳን መብት አላቸው፡፡ ማንም እኔ
ዐውቅላችኋለሁ ብሎ የእነርሱን ሟች ሊያተርፍላቸው
አይገባም፡፡›
‹ልክ ነው› አለ አንድ ፈርጣማ ጡንቻ ያለው ወጣት፡፡ ‹ሌላ
ብሔረሰብ አተርፋለሁ ብለን ገብተን ሳይተርፍ ቢቀር በኋላ
የብሔር ግጭት ያስነሣል፡፡ ማን ግቡ አላችሁ? ማን
ፈቀደላችሁ? ማን ወከላችሁ? ስንት ጥያቄ ይነሣል›
‹አንዴ ጠጋ ጠጋ በሉልኝ፡ ለፌስ ቡክ የሚሆን ፎቶ ላንሳ› አለና
አንዱ ገለል አደረጋቸው፡፡ ራቅ ብለው ጭቅጭቁን ቀጠሉ፡፡
ልጁ ጀልባዋ ስትሰምጥ የሚያሳይ ፎቶ አንሥቶ በፌስ ቡክ
ለቀቀ፡፡ በአንድ ጊዜ ሺ ላይክ አገኘ፡፡
‹እኔ ሄድኩ› አለ አንድ ልጅ፡፡ ‹ዝም ብዬ ነው የደከምኩት፡፡ የኛ
ብሔረሰብ ተወካይ ከሚሰምጡት መካከል የለም፡፡›
‹ሌሎቹን ለምን አታግዝም› አለው ልጅ እግሩ፡፡
‹የራስን ዕድል በራስ መወሰን ምን እንደሆነ አልገባህም›
አንድ ሁለት ሐሳቡን የተቀበሉ ወጣቶችን ይዞ ሄደ፡፡
‹እናንተ ስለ ብሔር ብቻ ነው የምታስቡት፡፡ የሴቶችስ ጉዳይ?
የሃይማኖትስ ጉዳይ?› አለና አንዱ አፋጠጣቸው፡፡
‹ልክ ነው፤ የተረሳውን ነው ያስታወስከን፡፡ ጀልባዋ ውስጥ ልዩ
ልዩ እምነቶችን የሚወክሉ ሰዎች አሉ፡፡ የሴቶችም ተዋጽዖ
ሊታሰብ ይገባል›
‹አሁን ችግር ሊገጥመን ነው፡፡ ሴቶች በአካባቢያችን የሉም፡፡
ሴቶቹን ማን ሊያወጣቸው ነው?›
‹ለምን እኛ አናወጣቸውም፤ የሴቶች ጉዳይ የሴቶች ብቻ ነው
እንዴ› አለ ያ ልጅ እግር
‹አንተ ልጅ ቀደም ቀደም አትበል? የሴቶችን ጉዳይ ወንዶች
የሚወስኑበት ዘመን አልፏል፡፡ ሴቶች የራሳቸውን ጉዳይ
እንዲወስኑ መፍቀድ አለብን፡፡
‹ቀላል ነው፡፡ ለሴቶች ሊግ ወይም ለሴቶች ማኅበር ወይም
ለሴቶች ሚኒስቴር ለምን አናሳውቅም፡፡ ሴቶች እየሰመጡ
ነውና አስፈላጊ ሁሉ ይደረግ ለምን አንልም›
አጨበጨቡ፡፡
‹እሺ ጀልባዋ ውስጥ ምን ምን ዓይነት እምነቶች አሉ› አለ
ጎልማሳው
‹እምነቶች የሉም፤ አማኞች ናቸው ያሉት› አለ ልጅ እግሩ፡፡
‹የሚወክሉትን እምነት ነው የፈለግነው›
‹ማን ወከላቸው፤ ለራሳቸው አመኑ እንጂ›
‹ነገርንህኮ፤ ችግር እስኪፈጠር ይወክላሉ፡፡ ችግር ከተፈጠረ
አይወክሉም›
‹መረጃው ፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው ያለው›
‹ጥሩ አንድ ኮሚቴ ይቋቋምና መረጃውን ይዞ ይምጣ› አለ
ጎልማሳው፡፡ ብዙዎቹ ተስማምተው ኮሚቴ አዋቅረው ወደ
ፌዴሬሽን ምክር ቤት ላኩ፡፡
ሌሎች ደግሞ ስለ ሴቶች ጉዳይ ሊያስረዱ ሄዱ፡፡
ሌሎቹ ሰው ያልተገኘላቸው ብሔረሰቦች፣ ከመካከላቸው
መርጠው ነፍስ አድን እንዲልኩ ለመንገር ሄዱ፡፡
ሌሎቹ ደግሞ የየሃይማኖቱ መሪዎች ሰው እንዲወክሉ
ለመንገር ተሠማሩ፡፡
የቀሩት ሰዎች ዋኝተው በመሄድ የሚሰምጡትን እንዳያወጡ
በፖሊስ ወደቡ ይጠበቅ ጀመር፡፡ በአወጣጣቸው ላይ አድልኦ
ከተፈጸም የብሔር ግጭት እንዳይነሣ ተፈርቷል፡፡
በዚህ መካከል ጀልባዋ ሙሉ በሙሉ ሰመጠች፡፡

Saturday, February 9

ወላይተኛ ቋንቋ እና ወላይታ /በኢትዮጵያና በደቡብ


'''➊✍ወላይትኛ''' በ[[ኢትዮጵያ]] በተጠቃሚ ብዛት በ4ኛነት የሚመደብና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሌሎቹ ተቀራራቢ ቋንቋዎች ምንጭ ነው። ወላይትኛ ከሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በፊት የመጀመሪያው የ[[ላቲን ፊደል]] [[መጽኃፍ ቅዱስ]] ታትሞበታል። ከወላይትኛ ጋር ዝምድና ያላቸው ሌሎች ቋንቋዎች [[ጋሞ-ጎፋ-ዳውሮ]] እና ኩሎና ኮንታ ናቸው። ባሁኑ ጊዜ በሥልጣን ላይ ያለው የ[[ኢሕአዴግ]] መንግሥት እነኚህን ተቀራራቢ ቋንቋዎች ነገር ግን 25% ትርጓሜዎቻቸው እርስ በርሳቸው በፍጹም የማይገናናኙትን <ዎጋጎዳ> በማለት አዲስ ስያሜ በመስጠት የ1ኛ ደረጃ መማሪያ መጽሃፍ አዘጋጀ። ይሁን እንጂ በተለይ በወላይታ ተወላጆች ዘንድ ኃይለኛ ቁጣን አስነስቶ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን በማጣታቸው ጉዳዩ የዓለምን ትኩረት ስቦ ነበር። ለምሣሌ ያህል፡ <ኦታ> ማለት በወላይትኛ ሥራ ማለት ሲሆን በጎሙኛ ግን [[ግብረ ሥጋ ግንኙነት]] የሚል ትርጓሜ ስላለው ለኅብረተሰቡ ያልተለመደና እጅግ አስነዋሪ ቃል ነው። <ቦግስ> ማለት በወላይተኛ አፍጥኗል ሲሆን በዳውሮኛ [ሩካቤ ስጋ ፈፅሟል] የሚል ትርጓሜ ይሰጣል። በአንጻሩ ግን አብዛኛው ቃል ቢመሳሰልም በመጽኃፍ ደረጃ ታትሞ ለልጆች ትምህርት እንዲውል ገዢው መንግሥት በቂ ጥናት ስላላደረገ በቂ ግንዛቤ አልነበረውም። ተቀባይነት ሳይኖረዉም ቀረ ታርካዊ ስህተትም ተደርጎ ይወሰዳል። ወንድማማቾች እና እህታማቾች የሆኑ ወላይታ ፣ጋሞ፤ጎፋና ዳዉሮ ህዝቦችንም አቃቅሯል።ሆኖም ወላይታዎች ወላይተኛን የአፍ መፍቻና ሥራ ቋንቋ አድርገው የቀጠሉት ከብዙ መስዕዋትነት በኃላ ነዉ። አማረኛ፣ኦሮምኛንና ሶማሊኛን ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ የሚገኘው ወላይተኛ ቋንቋ ከሌሎች ደቡብ ብሔረሰቦች ቋንቋዎች ግን ግንባርቀደም ነው። {{መዋቅር}} [[መደብ:ኦሞቲክ ቋንቋዎች]] ➋✍ወላይታ በቀድሞ ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ባሁኑ ደቡብ ክልል የሚገኝ ና የራሱ የሆነ ቋንቋና ባህል ያለው ሕዝብ ሲሆን ከ ሲዳማ፡ ከ ከምባታ፡ ከ ሃዲያና ተመሳሳይ ቋንቋ ከሚናገሩ ከ ኩሎ ኮንታ ከ ጎፋና ጋሞ ሕዝብ ጋር ይዋሰናል። ወላይታ ህዝቡ በጣም የተደባለቀ(ዉስብስብ) ሲሆን በከተማ አከባቢ ልቆ የሚገኝ ኃይማኖት ኦርቶዶክስ ይሁን እንጂ በጠቅላላ አውራጃው ፕሮቴስታንትና እስልምና እምነት እየተስፋፋ ነው። የወላይታ ዞን አስራ ሁለት ወረዳዎች አሉት። እነሱም፦ 1ኛ - ዳሞት ጋሌ ዋና ከተማው ቦዲቲ፡ 2ኛ -ዳሞት ወይዴ ዋና ከተማው፦ በደሳ፡ 3ኛ -ቦሎሶ ሶሬ ዋና ከተማው አረካ፡ 4ኛ - ሁምቦ ዋና ከተማው ጠበላ፡ 5ኛ - ኦፋ ዋና ከተማው ገሱባ፡ 6ኛ- ሶዶ ዙሪያ ዋና ከተማው ሶዶ፡ 7ኛ- ኮይሻ ዋና ከተማው በሌ፡ 8ኛ- ቦሎሶ ቦምበ ዋና ከተማው ቦምበ እድገት፡ 9ኛ- ዳሞት ሶሬ ዋና ከተማው ጉኑኖ፡ 10ኛ- ዱጉና ፋንጎ ዋና ከተማው ቢጣና፡ 11ኛ ዳሞት ፉላሳ ዋና ከተማው ሻንቶ፡ እና 12ኛ ኪንዶ ዲዳዬ ዋና ከተማው ሀላለ ናቸው። ወላይታ ከደቡብ ካሉት አከባቢዎች በትምህርት፡ በልማትና በማህበራዊ ሁኔታዎች ልቆ ሊገኝበት የቻለበት ሁኔታዎች ይታያል። ይህም የሆነበት ምክንያት በ ቀደማዊ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ምዕራባዊያን በብዛት ገብተው የአከባቢውን ሕዝብ ከ መጽሓፍ ቅዱስ ጋር የቀለም ትምህርት አጣምረው ስለሰጡ እድሉን በመጠኑም ቢሆን በመጠቀማቸውና በየጊዜው በአከባቢው የሚመደቡ አስተዳዳሪዎች ጠንካራ በመሆናቸው ነው ይባላል። በቀድሞ ዘመን በወላይታ በርካታ ምሁራን ብቅ ብቅ ብለው ነበር። ከነዚህም ምሁራን በደቡብ ኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ዶክተርና የጦር ጄኔራል ለመሆኑ የበቁ ብ/ ጄኔራል ዶ/ር ጋጋ ኤልጆ በአብይነት ሲጠቀሱ ፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ካንገት በላይ ስፔሻሊስት ዶ/ር ታዲዮስ ሙንኤ ; ኢትዮጵያ ካሏት ጥቂት የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ቀለሙ ደስታ ፡ አሜሪካን አገር በ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ፍሎሪዳ ታዋቂ ሓኪምና ረዳት ፕሮፌስር የሆኑ ዶ/ር ይስሓቅ ዳልኬ ናቸው።[1] ዶ/ር ይስሓቅ በትምህርት ውጤታቸው ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ልቀው በመገኘታቸው ከአጼ ኃይለስላሴ እጅ የወርቅ ሰዓት የተሸለሙ 2ኛው የወላይታ ተወላጅ ሲሆኑ ዳዊት ጦሼ ደግሞ የመጀመሪያው ናቸው። የወላይታ ታሪክ ሲወሳ የወላይታ የልማት አባት በሚል የሚታወቁ ዳጃ/ች ወ/ሰማዕት ስም ሁሌም አብሮ ይወሳል። ደ/ች ወ/ሰማዕት በአስተዳዳሪነት በቆዩበት በአጼ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ብዙ የልማት ስራዎችን አከናውነዋል። ከሰሯቸው አበይት ስራዎቻቸውም ፦ በጊዜው የነበሩትን ሰባቱንም ወረዳዎች የሚያገናኝ መንገድ አሰርተዋል። በሚሲዮናዊያን አማካኝነት የመጀመሪያውን የደቡብ ሆስፒታል አስገንብተዋል። ወላይታን ከምዕራብ ኢትዮጵያ የሚያገናኝና 90 ሜትር ርዝመት ያለውን ታሪካዊውን የኦሞ ድልድይ አሰርተዋል። ወጣቱ ትርፍ ጊዜውን የሚያሳልፈበትን ወወክማ የወጣቶች መንደር ከዘመናዊ በተ-መጻሕፍት ጋር አሰርተዋል። በሶዶ ከተማ ዘመናዊ የገበያ አዳራሽ ከማሰራታቸው ነው። ከይርጋለም ቀጥሎ በደቡብ የመጀመሪያውን ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አሰርተዋል። ደ/ች ወ/ሰማዕት በወቅቱ ማንም ወጣት የሆነ መንገድ ዳር ቆሞ ሲያወራ ካዩ ይበሳጩ እንደነበርና ከመኪናቸው ወርደው ስራ እንዲሰሩ ወይም ት/ቤት እንዲሄዱ ይመክሩም እንደነበር ይነገርላቸዋል። ባሁኑ ጊዜ ባገር ውስጥና ከአገር ውጭ በተሳተፉበት የሙያ ዘርፍ ሁሉ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር አንቱታን የተጎናጸፉ የወላይታ ተወላጆች ብዛት በርካታ ነው። አቶ ቦጋለ ዋላሎ እና ዋና ዋጌሾ በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ትምህርትን ያስፋፉ የወላይታ ተወላጆች ናቸዉ።

Featured Posts

“ግብፅ ግድቡን የሚመታ ራፋል የተባለ የጦር አውሮፕላን ገዝታ ነበር” የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም የተወለዱት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ የጁ ወረዳ በምትገኝ አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው። የልጅነት ጊዚያቸው...

Blogger